Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በዋና መስሪያቤቱ ለሚያስገነባው ሁለገብ ማዕከል (የንግድና የመኖሪያ)ህንፃ የዲዛይን ጥናትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ውይይት አካሄደ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) ባደረጉት የመግቢያ ንግግር ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ተልእኮ እውን ለማድረግ ባለው የሰለጠነ የሰው ሀይል የባቡር ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ለአገልግሎት በማብቃት በሀገራችን በተለይ በትራንስፖርት እና በጭነት ዘርፍ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል ፡፡

የባቡር ፕሮጀክት በባህሪው ብዙ መዋዕለ ንዋይ የሚፈልግ በመሆኑ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ምንጮችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ ገልጸው ለዚህም በዋናመስሪያ ቤቱ ባለ ሰፊ ቦታ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ማዕከላትን (Multi- purpose complex buildings) ለመገንባት እቅድ ይዞ በአማካሪ ድርጅቱ የተዘጋጀው ጥናት ላይ ተመስርቶ የባለድርሻ አካላት ግብአት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ትልቅ ይዞታ እንዳለው እና የሚገኝበት አካባቢም በመሀል ከተማ በመሆኑ በተጨማሪ ጎብኝዎችን የሚስቡ ቦታዎች መስቀል አደባባይ፤ ኦሮሚያ የባህል ማእከል እንዲሁም የቀድሞ ባቡር ጣቢያ(ሼ-መንደፈር) በአካባቢው መኖራቸው የበለጠ ተመራጭ ሁለገብ ማዕከል እንዲሆን የሚያደርገው መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ጥናቱ የተዘጋጀው በ Rail Transit Engineering Consultancy (CRTEC) ሲሆን ጥናቱን ያቀረቡት በአማካሪ ድርጅቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ናትናኤል ይስሀቅ ስለ ፕሮጅክቱ ምንነት እና ይዘት በዝርዝር ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና አስተያቶች ተነስተው መልስ እና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡



Leave a Reply