Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

አዲስ አበባ ቀላል ባቡር (AALRT)

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ከሰሜን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ-አውቶቡስ ተራ-ልደታ -መስቀል አደባባይ ቃሊቲ ድረስ 16.9 ኪ.ሜ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ከሀያት የመኖሪያ መንደር -መገናኛ-መስቀል አደባባይ-ወደ ጦር ሀይሎች የሚሄድ መስመር 17.35 ኪ.ሜ በአጠቃላይ 34ኪ.ሜ ርዝመት ፤ 1.435 ሜ. ስታንዳርድ ጌጅ ስፋት እና ባለሁለት ትራክ/ሀዲድ/ ነው፡፡ ሁለቱም መስመሮች ከመስቀል አደባባይ እስከ ልደታ ቤተክርስቲያን ድረስ 2.7 ኪ.ሜ ያህል ርዝመት ያለው ሀዲድ በጋራ ይጠቀማሉ፡፡

በሰዓት 80 ኪ.ሜ የመጓዝ አቅም ያለው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መስመር በሙሉ የግንባታ ሥራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን በቀን በአማካይ 120ሺ ተሳፋሪዎችን እያጓጓዘ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ችግር በሰፊው ከመቅረፉም በተጨማሪ ለከተማዋ ውበት እና መልካም ገፅታ ግንባታ የጎላ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

0
Built at cost of 475 million US dollars.

How can we help you?

Contact us at the Ethiopisn Railway Corporation Headoffice or submit a business inquiry online