Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

/ኢምባኮ 03/13/2015 ዓ.ም/ 

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎች የ2016 አዲስ አመት ዋዜማን አስመልክቶ የጳጉሜን ቀናት በልዩ ልዩ ኘሮግራሞች አከበሩ፡፡

የኮርፖሬሽኑን የ2015 በጀት አፈጻጸም እና የ2016 በጀት አመት ዕቅድ በኮርፖሬሽኑ የባቡር ኔትወርክ ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ስለሢ ካሻ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው በሠጡት የሥራ አቅጣጫ በ2015 በጀት አመት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት አመርቂ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ በጀት አመት በበለጠ የሥራ ተነሳሽነት ያሉብንን ተግዳሮቶችን መፍትሄ በመስጠት የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ተቋሙን ተወዳዳሪ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን ያሉ ሲሆን ለዚህም የሁሉም ሰራተኞች ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ 

የአገልግሎት ቀንን በማስመልከት ኮርፖሬሽኑን አገልግለው በ2015 ዓ.ም በጡረታ ለተሰናበቱት የሶሻል ኮሚቴ አባላት ወ/ሮ ገነት አሰፋ፣አቶ ፀጋዬ ቢረዳ እና አቶ ንጉሴ ኤደቻ እንዲሁም ከኮርፖሬሽኑ ወደ ሌላ ተቋም ለተዛወሩት ለአቶ ሄኖክ ቦጋለ የሽኝት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡ በዚሁ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው ስላገለገላችሁን እናመሰግናለን፡፡ ብለዋል፡፡

የበጐነት ቀንን በተመለከተም ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለአረጋውያንና ህጻናት ድጋፍ የሚውል የአንድ መቶ ሺህ ብር እና ከኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የተሰባሰቡ የአልባሳትና የጫማዎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የሜሪ ጆይ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ ለተደረገላቸው ድጋፍ በተረጂዎቹ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ 

በተያያዘ ዜና በኮርፖሬሽኑ የስርዓተ-ፆታ እና ማህበራዊ ጉዳይ የስራ ክፍል አስተባባሪነት በኮርፖሬሽኑ በጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች ድጋፍ ለሚደረግላቸው በኤች አይ ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት የደብተር መያዣ ቦርሳና ጫማ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን ለአሳዳጊዎቻቸው ኢኮኖሚቸውን የሚያሻሽሉበት የስራ ማስጀመሪያ ቁሳቁስ ተበርክቶላቸዋል፡፡

         



Leave a Reply