Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

/ኢምባኮ 21/01/2016ዓ.ም/ 

ኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት የስራ ዘርፍ መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም አስጀመረ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የተቋሙ ክንውኖች በመረጃ አያያዝ ሥርዓት በManagement Information System (MIS) የታገዘ እንዲሆን ለማድረግ ሲከናወን የነበረው ጥናት ተጠናቆ እዚህ በመድረሱ ስራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወጥነት ባለው መልኩ እንዲከናወኑ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡

ይህ ጥናት እዚህ እንዲደርስ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና አቅርበው ለውጤታማርነቱም ተከታታይ ስራ እና ጥረት ይፈልጋል ብለዋል፡፡ በቀጣይ የሰው ሀብት እና የግዢ አሰራ ስርዓት በዚህ መልኩ ተጠናቀው ወደ ትግበራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል፡፡Leave a Reply