Ethiopian Railways Corporation

ቋንቋ

ውይይቱ ሁለቱ ሀገራት አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ሲሆን የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በባቡር መሠረተ ልማት፤በባቡር ትራንስፖርት እንዲሁም በሎጂስቲክስ እና መልቲ ሞዳል ስራዎች ላይ መሰማራት በሚችሉበት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በመልቲ ሞዳል ስራዎች ላይ የተሰማሩ የፈረንሳይ ተቋማት በኢትዮጵያ ሊሳተፉ በሚችሉበት ሁኔታ፤በሀገራችን በቀጣይ ሊገነቡ በእቅድ በተያዙ የባቡር መሠረተ ልማቶች መንግስት ባስቀመጣቸው አማራጮች ላይ፤በተለያዩ የፋይናንስ አማራጮች ከተለያዩ የኢትዮጵያ የባህር በሮች ጋር የሚያገናኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የትኩረት መስመሮች ናቸዉ፡፡ እነርሱም ሞጆ- ሞያሌ- ላሙ ወደብ (ላኘሴት ኮሪደር) ኬንያ፤ድሬዳዋ- በርበራ- ሶማሌ ላንድ፤ወልዲያ-መተማ- ፖርት ሱዳን (ሱዳን)፤ ከወልዲያ መቐሌ የባቡር መስመር ወደ ኤርትራ ወደብ (አሰብ/ምጽዋ) የፈረንሳይ ባለሀብቶች ሊሳተፉበት ስለሚችሉበት ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡



Leave a Reply