የዜና መግለጫ

በባቡር መስመር ግንባታ ኢትዮጵያውያን ዕውቀት እየቀሰሙ መሆኑ ተገለፀ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: በባቡር መስመር ግንባታ ኢትዮጵያውያን ዕውቀት እየቀሰሙ መሆኑ ተገለፀ
የተጫነበት ቀን:  1/24/2019 11:16:44 AM
የዜናው አካል:  በባቡር ምህንድስና በተለያዩ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ዘርፎች ውጤታማ የዕውቀት ሽግግር መኖሩን በአዋሽ-ወልድያ/ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት በተቋራጩና በአማካሪ ድጅቱ ውስጥ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ ባለሙያዎች ገለፁ፡፡ በሃሮማያ ዪኒቨርሲቲ ሶይል ወተር ኢንጂነሪግ ያጠናውና የአዋሽ-ወልድያ/ሃራገበያ የባቡር ፕሮጀክትና በአማካሪነት በሚያከናውነው የሲስትራ-መልቲዲ ውስጥ በሱፐርቪዥን ባለሙያነት እየሰራ የሚገኘው ኢ/ር ዳግማዊ ያሬድ ከዚህ በፊት በተለያዩ የሙያ መስኮች ላይና በአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ላይ መሳተፉን ገልፆ በዚህ ፕሮጀክት ላይም ልምዱን እንዳካበተና የቴክኖሎጅ ሽግግሩ ውጤታማ መሆኑን ገልጿል፡፡ መልቲዲ የተባለ ሃገር በቀል አማካሪ ድርጅት ሲስትራ ከተባለው የፈረንሳይ ካምፓኒ ጋር በጋራ መስራታቸውም ካምፓኒው ዓለም አቀፍና የካበተ ልምድ ያለው በመሆኑ የተሻለ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸውም ኢ/ር ዳግማዊ ገልጿል፡፡ በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ የሁለተኛ ድግሪያቸውን ያስተማራቸው ባለሙያዎች የስራ ላይ ስልጠና በሚወስዱበት ወቅት ለስድስት ወር ያህል ስልጠናውን መስጠት መቻላቸው የውጤታማነቱ አንድ ማሳያ መሆኑንና በሙሉ አቅም እየሰሩ መሆኑን ገልጿል፡፡ በኮንስትራክሽንና ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀችው ኢ/ር ረድኤት እርቅይሁን በግልገል ጊቤ 3 ሃይድሮፓዎር ፕሮጀክት ላይ መስራቷን ገልፃ በአሁኑ ሰዓትም በአዋሽ-ወልድያ ፕሮጀክት በኮንትራክተሩ ያፒ መርከዚ ውስጥ ሲኒየር ኳሊት ኮንትሮል ኢንጅነር በመሆን እየሰራች መሆኑን ገልፃለች፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ላይ መስራቷም አዳዲስ እውቀት ማግኘት እንደቻለች ገልፃለች፡፡ ለአብነትም ከመሰረተ ልማት ግንባታው በፊት በላብራቶሪ የሚሰሩ የጥሬእቃ ሙከራዎች( Material Test) እንዴት እንደሚሰራ፣ ሳይት ላይ የሚሰሩ ስራዎች እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረጉ፣ የባቡር ሃዲዱ ንጣፍ(ስሊፐር) በሚመረትበት ወቅት ያለውን ሂደት ፋብሪካ ውስጥ እንዴት እንደሚገጣጠምና ባቡሮች እንዴት እንደሚጠገኑ የመሳሰሉ ግንዛቤዎችን ማግኘት መቻሏን ኢ/ር ረድኤት ገልፃለች፡፡ በፕሮጀክቱ የመስራት ዕድል ማግኘቷም በትምህርት ቆይታ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ያገኘችውን እውቀት በተግባር ማየትና ተግባራዊ ማድረግ መቻሉ ለወደፊት በሚሰሩ ስራዎች የላቀ አስተዋፅኦ አለው ስትል ገልፃለች፡፡ በተጨማሪም በኮንትራክተሩ የተለያዩ ዲፓርትመንቶች ውስጥ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ተሳታፊ ቢሆኑ ለቴክኖሎጂ ሽግግሩ የበለጠ ውጤታማነት እንዲኖረው ያስችላል ስትልም አስተያየቷን ገልፃለች፡፡