የዜና መግለጫ

የኮርፖሽኑ ሰራተኞች የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: የኮርፖሽኑ ሰራተኞች የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ
የተጫነበት ቀን:  11/29/2018 2:57:23 PM
የዜናው አካል:  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሰራተኞች በዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ህዳር 15 ቀን 2011 ዓ.ም የፅዳት ዘመቻ አደረጉ፡፡ የፅዳት ዘመቻው ዋና ዓላማ የኮርፖሬሽኑን ቅጥር ግቢ ለስራ ምቹና ማራኪ ለማድረግ አመራር እና ሰራተኞች ያስተባበረ የፅዳት ዘመቻ የማድረግ ስራ በ100 ቀናት እቅድ ውስጥ የተካተተ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ህዳር 15 ቀን 2011 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ መካሄዱን በኮርፖሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ደረጀ ተፈራ ገልፀዋል፡፡ ይህ የፅዳት ዘመቻ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ያስጀመሩት ሲሆን ፅዳቱ የተካሄደው ኮርፖሬሽኑ ወደፊት ለቢሮ አገልግሎት በሚጠቀምባቸው ህንፃዎች አካባቢ ያሉ ቁጥቋጦዎች እና ደረቅ ቆሻሻዎችን በመመንጠር፣በማፅዳት እና በማቃጠል ላይ አተኩሮ ለአንድ ሰዓት ያህል የተከናወነ መሆኑን አቶ ደረጀ አስታውቀዋል፡፡ ይህ የፅዳት ዘመቻ የመጀመሪያ ቢሆንም በቀጣይ በበቂ ዝግጅት እና በቂ የፅዳ ቁሳቁሶችን በማሟላት እየተጠናከረ እንደሚሄድ እና በኮርፖሬሽኑ ምቹና ፅዱ የስራ አካባቢ ለመፍጠር በጋራ በመስራት ውጤት ማምጣት እንደሚቻል የታየበት ሲሆን ለወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ደረጀ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ዶ/ር ስንታየሁ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ለዚህ ተግባር ጊዜቸውን ሰውተው ላደረጉት አስተዋፅኦ በማመስገን ለቀጣይም ተባብሮ የመስራት ባህል መዳበር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡