የዜና መግለጫ

የቅድመ ጥናት ወርክሾፕ ተካሄደ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: የቅድመ ጥናት ወርክሾፕ ተካሄደ
የተጫነበት ቀን:  11/27/2018 11:58:44 AM
የዜናው አካል:  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በሚያቀቋርጥባቸው ቦታዎች የገቢ ማስገኛ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል የቅድመ ጥናት ወርክሾፕ ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ቢሮ ተካሄደ፡፡ በሀገራችን እየተገነባ ያለው የባቡር መሠረተ ልማት ከታዳሽ ሀይል በመሆኑ ከአየር ንበረት ብክለት ነፃ በመሆኑ አለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት በተፈጠረው ዕድል በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ለሚከናወኑ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ቅድመ ጥናት ለማድረግ ወርክሾፑ መዘጋጀቱን በኮርፖሬሽኑ የንግድ ስራዎች ማበልፀጊያ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሽዋንግዛው ክፍሌ ገልፀዋል፡፡ የአየር ንበረት ለውጥ ፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት ሁለት መንገዶች እንዳሉ የጠቀሱት አቶ ሸዋንግዛው እነዚህም ገበያ ተኮር ማለትም በምንለቀው መጠን ካርቦን መሸጥ እና ገበያ የሌለው ማለትም የምንጠቀመው የትራንስፖርት ዘዴ አረንጓዴ /ከካርበን ልቀት ነፃ ! በመሆኑ ብቻ የፋይናንስ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ ለሆኑ ሀገራት በማመልከት ገንዘቡ የሚገኝበት ዘዴዎች እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ አዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከካርበን ነፃ በመሆን ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ያስታወቁት አቶ ሽዋንግዛው እ.ኤ.አ.በ2015 ሲቲሲኤን /Climate Technology Center Network የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ በተጠየቀው መሠረት የኮርያ መንግስት ፍላጎት አሳይቷል ብለዋል፡፡ የኮሪያ መንግስት ገንዘቡን የሚሰጠው በሲቲሲኤን /Climate Technology Center &Network/ በኩል ሲሆን ለዚህም አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች ሲከናወኑ እንደነበር አቶ ሽዋንግዛው ተናግረዋል፡፡ የወርክሾፑ አላማም በአዲስ አበባ ሊሰሩ የታቀዱ የንግድ ስራዎች/TOD/ ለሚለቀቀው የፋይናስ ድጋፍ የንግድ ቦታዎች መረጣ ጥናት ለማድረግ የቅድመ ጥናት ስራዎች እንዴት እንደሚከናወኑ ለመወያየት መሆኑን አቶ ሸዋንግዛው አብራርተዋል፡፡ ጥናቱ ቀጣይ የባቡር ማስፋፊያዎችንና ሌሎች የከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፎችን ያካተተ በማስተር ፕላን የተደገፈ እንደሚሆን አቶ ሸዋንግዛው ጠቅሰው ከአዲስ አበባ ፕላን ኮሚሽንና አዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመነጋገር የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ የንግድ ቦታዎቹ መረጣ ሲደረግ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ያሟላ፣ለተሳፋሪዎች መረጃ የሚሰጥ ሆኖ ለቀጣይ 20ና30 ዓመታት ምን ሊሆን ይችላል በሚል የተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮችን ያማከለ ጥናት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ ይህንን ስራ ለመስራት የሚሰጠው ገንዘብ በቂ ስላልሆነ የኮርያ መንግስት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያደርግ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ጥናቱ ሁሉንም ትራንስፖርት አማራጮች በአንድ አካባቢ የሚያገናኝ ከሆነ የተሻለ የንግድ ለመስራት ያስችላል ያሉት አቶ ሸዋንግዛው እስካሁን ባለው ሂደትም ፕሮጀክት ፕሮፖል ለመስራት የሚያስችል ዝርዝር ሀሳብ በአዲሰ አበባ መስተዳደር በኩል ዳታ እየተሰበሰበ ይገኛል ብለዋል፡፡