የዜና መግለጫ

ኮርፖሬሽኑ በዘጠነኛው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ የመንገድና ባቡር መሰረተ ልማት ጉባኤ ተሳተፈ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: ኮርፖሬሽኑ  በዘጠነኛው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ የመንገድና ባቡር መሰረተ ልማት ጉባኤ ተሳተፈ
የተጫነበት ቀን:  10/16/2018 3:42:57 PM
የዜናው አካል:  ኮርፖሬሽኑ ኢትዮጵያን ወክሎ በባቡር ግንባታና ኦፕሬሽን ልምዱን ያካፈለበት ዘጠነኛው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ የመንገድና ባቡር መሰረተ ልማት ጉባኤ ‹‹ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት በትራንስፖርት ልማት›› በሚል መሪ ቃል እ.ኤ.አ ጥቅምት 9 እና 10 በታዛኒያ ዳሬሰላም ተካሄደ፡፡ ጉባኤው አንድ ዓለም ዓቀፍ ሁነት አዘጋጅ ከታንዛንያ መንግስት ጋር በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ዓለምአቀፍ ተቋራጮችና አማካሪዎች፣ የግል ባለሃብቶች፣ የትምህርት ተቋማት ተወካዮችና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በጉባኤው ሃገራችን ኢትዮጵያ በባቡር መሰረተ ልማት ግንባታና ኦፕሬሽን ላይ ልምድ እንድታካፍል የተጋበዘች ሲሆን የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን ወክለው ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በባቡር አካዳሚ ዘርፍ ተወካይ የምርምርና ስርፀት ሃላፊ የሆኑት ኢንጂነር ብሩክ ወንድሙ ሃገራችን ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ሃብት ከባቡር መሰረተ ልማት ዝርጋታ እድገት ጋር አጣምረው ገለፃ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከ100 ዓመት በፊት በባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ እና አገልግሎት በመስጠት ለባቡር ዘርፉ አዲስ ባትሆንም ዓለም በአሁኑ ወቅት ከደረሰበት ቴክኖሎጅ አንፃር የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታና ኦፕሬሽን ላይ ተግዳሮቶች እንደሚገጥሟት የሚጠበቅ ነው ሲሉ የገለፁት ኢ/ር ብሩክ ሆኖም ግን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርና የአዲስአበባ-ጅቡቲ ብሄራዊ ስታንዳርድ ጌጅ የባቡር ግንባታ አጠናቆ ወደ አገልግሎት መግባት መቻል ቀላል የማይባል ስኬት በመሆኑ ሃገራችን በባቡር ዘርፉ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ምሳሌ በመሆኗ ትልቅ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡ ኢ/ር ብሩክ በጥናታዊ ፅሁፋቸው በመንግስት በኩል ለዘርፉ ጠንካራ ፍላጎትና ቁርጠኝነት መኖሩ፣ በቂ የሰለጠነ የሰው ሃብት መኖሩ፣ በቅርቡ ኮርፖራሽኑ የሚያስገነባው እና የአፍሪካ የባቡር አካዳሚ የመሆን ራዕይ የሰነቀው የኢትዮጵያ የባቡር አካዳሚ አንዱ ማሳያ መሆኑ፣ በሁሉም ኮሪደሮች እያደገ የመጣ የጭነትና የመንገደኞች ፍላጎት፣ የግል ባለሃብቶች በዘርፉ PPP (Public Private Partnership) እንዲሳተፉ በመንግስት በኩል ፍላጎት መኖሩ ፣ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ንግድን ለማሳደግ ያለው ቀጠናዊ ትስስር፣ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ለመደገፍ ከልማት አጋሮች አዎንታዊ ምላሽ መኖሩ፣ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጅ ባቡርን አንድ አካል ማድረጉ፣ የኢንደስትሪ ፓርኮች፤ ግብርናና ኢንደስትሪን የሚያስተሳስሩ ፓርኮችና ማዕድናት የባቡር መስመሩ ኮሪደሮች ላይ መገኘታቸው የመሳሰሉ በቀጣይ በባቡር ፕሮጀክቶች በአጋርነት ለመስራት የሚያስችሉ መልካም አጋጣሚዎች(Opportunities) መኖራቸውን በጉባኤው ገልፀዋል፡፡