የዜና መግለጫ

ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት መስጠት ጀመረ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት መስጠት ጀመረ
የተጫነበት ቀን:  7/19/2018 10:28:48 AM
የዜናው አካል:  በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ነጂዋች ባነሱት የጥቅማጥቅም ጥያቄ ጋር በተያያዘ በትላንትናው እለት ለሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ገለጹ፡፡ የትሬን ማስተሮቹ ባነሷቸው የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ዙሪያ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከሰራተኞቹ ጋር የተወያዩ መሆኑን አቶ ደረጀ ገልጸው በተነሱ ጥያቄዎች መግባባት ላይ መድረስ በመቻሉ ተቋርጦ የነበረው የባቡር ትራንስፖርት አገልገሎት ከሐምሌ 11 2010ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ጀምሮ በከፊልና ሐምሌ12 2010ዓ.ም ከጥዋቱ 12፡00 ጀምሮ ከትሬይን ማስተሮች ጋር በተደረሰ መግባባት ከሰሜን-ደቡብ ስምንት (8) ባቡሮች ከምስራቅ-ምዕራብ አስራአንድ(11) ባቡሮች በድምሩ አስራ ዘጠኝ (19) ባቡሮች አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የትራንስፖርት አበል ብር 500 የሙያ አበል ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ላላቸው/Certified/ለሆኑ፣ የባቡር ማስተር አስተባባሪዎች ብር 1500 እንዲሁም ለቴክኖሎጂ አስተባባሪዎች፣ ለኮምፕርሄንሲብ አስተባባሪዎች፣ ለOCC dispatching and depot dispatching አስተባባሪዎችና ተጓዳኝ አስተባባሪዎች በወር ብር 1000 እንዲከፈላቸው ማናጅመንቱ ወስኗል፡፡ በተጨማሪም ለስራ ማነቃቂያ አበል ለደረጃ1 ባለሙያዎች ብር1500፣ ደረጃ 2 ባለሙያዎች ብር700፣ ደረጃ 3 ባለሙያዎች ብር400 እና የፈረቃ አበል(shift allowance) የሚከፈላቸው ሲሆን እንዲሁም ከሐምሌ 1ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን የተወሰነውን የባቡር ትሬይንማስተሮች እንዲያውቁ ተደርጓ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለካፍቴሪያ የምግብ ድጎማ 50%፣ የባቡር ትራንስፖርት በነፃ፣ የህክምና አመታዊ ወጪ ብር10,00ና የ24 ሰዓት የህይወት ኢንሹራንስ ተግባራዊ እየተደረገ የነበረው በነበረበት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መድረስ መቻሉን አቶ ደረጀ ተፈራ ገልፀዋል፡፡