የዜና መግለጫ

በኮርፖሬሽኑ የስራ አሰራር ስርዓት መስፈርት(SOP) ዝግጅት ገለፃ ተካሄደ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: በኮርፖሬሽኑ የስራ አሰራር ስርዓት መስፈርት(SOP) ዝግጅት ገለፃ ተካሄደ
የተጫነበት ቀን:  5/23/2018 3:21:34 PM
የዜናው አካል:  ኮርፖሬሽኑን በISO 9001, 2015 የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ብቁ ለማድረግ የስራ ክፍሎች የሚያዘጋጁትን የስራ አሰራር ስርዓት መስፈርት በተመለከተ በኮርፖሬሽኑ የሰራተኞች ክበብ ለተገኙ የኮርፖሬሽኑ መምሪያ ሃላፊዎች ገለፃ ተደረገ፡፡ በኮርፖሬሽኑ ያሉ የስራ ክፍሎች የየራሳቸውን የስራ አሰራር ስርዓት መስፈርት እንዲያዘጋጁ የሚያስችል ቅፅና ናሙና ተዘጋጅቶ በማኔጅመንት የፀደቀ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ገለፃውን ያቀረቡት የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ማሻሻያ ፕሮጀክት ኮሚቴ የሆኑት ወ/ሮ ሔዋን ጌታቸው ሁሉም የስራ ክፍሎች የስራ አሰራር ስርዓት መመሪያ ሊኖራቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በገለፃው የፕሮጀክቱ ጠቀሜታ በተመለከተም ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ አካባቢ ለመፍጠር፣ ሠራተኞች በተሻለ መንገድ ስራዎችን ለማከናወን እንዲነሳሱ እንዲሁም አንድን ስራ በትክክለኛ መንገድ ለማስኬድ ያግዛል ሲሉ ወ/ሮ ሄዋን ገልፀዋል፡፡ በስራ አሰራር ስርዓት መስፈርት መሰረት መስራት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የኮርፖሬሽኑን አሰራር መቀየር እስከተፈለገ ድረስ አስገዳጅ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ISO ሰርቲፋይ ማድረጉ እንዳለ ሆኖ የመስሪያ ቤቱ የአሰራር መመሪያ መኖሩ ስራዎች እንዴት መሰራትና ምን መሰራት እንዳለበት ለማወቅም የሚስችል መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ከታዳሚዎች የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ማንዋሉ የሚዘጋጅበት ቋንቋ በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ ከዜጎች ቻርተር በስተቀር ሁሉም ማንዋሎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ እንደሚዘጋጁ በማኔጅመንቱ መወሰኑን የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጅነር ቢኒያም አያሌው የገለፁ ሲሆን በቀጣይ እንደየስራክፍሎቹ ባህሪ ወደ አማርኛ ቋንቋ እንደሚተረጎም አሳውቀዋል፡፡