የዜና መግለጫ

ጃንግ ዘንግያን ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰሩ የባቡር መስመሮችን ጎበኙ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: ጃንግ ዘንግያን ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰሩ የባቡር መስመሮችን ጎበኙ
የተጫነበት ቀን:  5/15/2018 2:52:58 PM
የዜናው አካል:  የቻይና የባቡር ምህንድስና ግሩፕ/CREC/ ፕሬዝደንት ሚስተር ጃንግ ዘንግያን ኢትዮጵያ ውስጥ በቻይና መንግስት ትብብር የተሰሩ የባቡር መስመሮችን ግንቦት 02 ቀን 2010 ዓ.ም ጎበኙ፡፡ ሚ/ር ጃንግ ከሰበታ-ሜኢሶ የተዘረጋው የባቡር መስመር ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልፀው በቀጣይም ከኮርፖሬሽኑ ጋር ተቀራርበው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታም የቻይና ህዝባዊ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርና አፈ-ጉባኤ ሚስተር ሊዣንሹ ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ.ም ለቡ የሚገኘውን የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት እና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤቶችን ጎብኝተዋል፡፡ አፈ-ጉባኤው በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የተዘጋጀው የፎቶ ኤግዚቢሽን ከጎበኙ በኋላ ከቃሊቲ-ስታዲየም ድረስ በባቡር በመጓዝ የጉብኝታቸው ፍፃሜ አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ላለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የልማት ዕቅዶች ቻይና የምታደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልፆል፡፡