የዜና መግለጫ

ኮርፖሬሽኑ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: ኮርፖሬሽኑ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
የተጫነበት ቀን:  5/9/2018 2:25:26 PM
የዜናው አካል:  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በመስራት ላይ ላሉ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በባቡር አካዳሚ እሰጠ መሆኑን አስታወቀ፡ በባቡር አካዳሚው የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሲሳይ ጉታ የስልጠናው ዋና ዓላማ ባለሙያዎቹ ወደ ዘርፉ ከመግባታቸው በፊት ኢንዱስትሪ ተኮር ስልጠና ተሰጥቶአቸው ወደ ስራ ሲሰማሩ በዘርፉ ውጤታማ ስራን እንዲያከናውኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው የንድፈ ሀሳብ ፈተና ካለፉ በኋላ ወደ ተግባር ስልጠና እንደሚገቡ ከተግባር ስልጠናው በኋላም ተፈትነው ወደ ስራ እንደሚሰማሩ ወ/ሮ ሲሳይ ጠቅሰው ይህም ሙያው የሚጠይቀውን ደረጃ ያሟሉ፤ ብቁና ተወዳዳሪ ሰራተኞች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡ እስካሁን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በኮንትራት ማናጅመንት በሁለት ዙር የተሰጠ ሲሆን አሁን ግን ባቡር አካዳሚ ኃላፊነቱን ወስዶ በሁለት ዲፓርትመንቶች ላይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ወ/ሮ ሲሳይ ገልፀዋል፡፡ የመጀመሪያ ስልጠና ሮሊንግ ስቶክ ጥገና /Rolling stock maintenance/ ላይ የሚያተኩር ሲሆን 15 ሰልጣኞች አሉ፤ሁለተኛው ደግሞ ስለሀይል ስልጠና የሚሰጥ/Power/ ሲሆን በዚህ ዘርፍም 17 ሰልጣኞች እንዳሉ ወ/ሮ ሲሳይ ገልፀዋል፡፡ የንድፈ ሀሳብ ስልጠናው በባቡር አካዳሚ ከተሰጠ በኋላ በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ዋና መስመር ላይ የተግባር ስልጠናውን ለሶስት ወር ይወስዳሉ ያሉት ወ/ሮ ሲሳይ እነዚህን ስልጠናዎች ሲያጠናቅቁ ብቁ ሆነዋል ተብለው በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ቅጥር እንደሚፈፀምላቸው ገልፀዋል፡፡ ሰልጣኞቹ በመካኒክ፣ በኤሌክትሪክሲቲ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ በሜካትሮኒክስ እንዲሁም አውቶሞቲቭ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶች በደረጃ 2 እና 3 የሰለጠኑ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ባቡር ከፍተኛ ካፒታልና ባለሙያ የሚያስፈልገው ኢንዱስትሪ በመሆኑ ማንኛውም ኦፕሬተር ወይም ቴክኒሻን ወደ ስራው ከመግባቱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የጠቆሙት ወ/ሮ ሲሳይ ይህም ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳዋል ብለዋል፡፡ ስልጠናው እየተሰጠ ያለው በራስ አቅም ሲሆን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ማነጅመንት ኮንትራክተር ጋር በረዳት አሰልጣኝነት የሚሰሩ መምህራን እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመርቀው ስራ ላይ ባሉ መሀንዲሶች እየተሰጠ መሆኑን ተናረዋል፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግር በእውቀት አኳያ ሲታይ መምህራኑ በቅርበት ከማነጅመንት ኮንትራክተሩ ጋር ሲሰሩ የነበሩ ስለሆኑ ሙሉ በሙሉ ስልጠናውን መስጠት እንችላለን ብለው በመስጠት ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ወ/ሮ ሲሳይ እስካሁንም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣም ማኔጅመንት ኮንትራክተሩ ስራውን ማስረከቡ ስለማይቀር ስልጠናዎች ሙሉ በሙሉ በባቡር አካዳሚ ለመስጠት ላሉት መምህራን አቅም የማሳደግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ወ/ሮ ሲሳይ ጠቅሰው ከዚህም ባለፈ ለተያዩ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶችም ጭምር ስልጠናዎችን ለመስጠት ስልት በመንደፍ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ እንዳለ ገልፀዋል፡፡ ኢ/ር ክብሩ ደሊል በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከፍተኛ ቴክኒሻን ሲሆን ድርጅቱ ባመቻቸው የስልጠና መርሀ-ግብር ለአሰልጣኝነት ተወዳድሮ በማለፉ ለአዳዲስ ባለሙያዎች ስልጠና እሰጠ መሆኑን ይናገራል፡፡ ድርጅቱ ባመቻቸው የትምህርት ዕድል በውጭ ሀገር ያገኘው እውቀት እዚህ በመተግበር ላይ እንደሆነ ፤ ይህንን እውቀት ለአዳዲስ ባለሙዎች እያስተላለፈ መሆኑና ሽግግሩ ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ ኢ/ር ክብሩ ገልፆ ነገር ግን የተግባር ስልጠናውን የሚያግዙ መሳሪዎች በቂ ባለመሆናቸው ተቋሙ ለዚህ ትኩረት ሰጥቶ የሚሟላበትን መንገድ ማመቻቸት አለበት ብሏል፡፡ በተጨማሪም ‘‘ለአሰልጠኝ መሟላት ያለባቸው ጥቅማጥቅሞች የሉም እነዚህ ቢስተካከሉ ጥሩ ነው’’ ሲል ተናግሯል፡፡ ሺመልስ ወንድሙ ከቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በሜካትሮኒክስ ሙያ ሰለጠነ ሲሆን አሁን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በሰብስቴሽን ቴከኒሻንነት እየሰለጠነ ይገኛል፡፡ ለድርጅቱ አዲስ መሆኑ እንዲሁም ቴክኖሎጂውም ለሀገሪቱ አዲስ በመሆኑ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ በመሆኑ ደስተኛ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ በመሆኑ ከስልጠናው በኋላ በራስ አቅም ለመስራት የሚያስችል እውቀት እያገኘ እንዳለ ተናግሯል፡፡ አሸናፊ ክፍለዮሀንስ ከመቀለ ዩኒቨርስቲ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተመርቆ በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ጀማሪ ሰብስቴሽን ኢንጂነር ስልጠና እየወሰደ ይገኛል፡፡ ‘’ስልጠናው ጥሩ ነው በሀገራችን ባለሙያዎች መሰጠቱ ደግሞ የተሻለ እንዲሆን ያደርገዋል’’ ሲል ተናግሯል፡፡ የቋንቋ ክፍተት አይኖርም ያልገባንን ጠይቀን በቀላሉ መረዳት እንችላለን በራስ አቅም ለመስራትም የሚስችል እውቀት እንዳ የጠቀሰው አቶ አሸናፊ የተግባር ስልጠናው ላይ ያልተሟሉ መሳሪያዎች ስላሉ መስተካከል አለበት ብሏል፡፡