የዜና መግለጫ

ኮርፖሬሽኑ MISን ለመተግበር ለሱፐርቫይዘሮች ስልጠና ሰጠ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: ኮርፖሬሽኑ MISን ለመተግበር ለሱፐርቫይዘሮች ስልጠና ሰጠ
የተጫነበት ቀን:  2/23/2018 4:50:54 PM
የዜናው አካል:  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የMIS ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ከየስራ ክፍሉ ለተውጣጡ 23 የፕሮጀቱ ሱፐርቫይዘሮች በኮርፖሬሽኑ የባቡር አካዳሚ የስልጠና አዳራሽ ለሁለት ሳምንታት ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናው የካቲት 5 ጀምሮ ለሁለት ሳምንት የቀጠለ መሆኑን የገለፁልን የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አክሊሉ ብዙአየሁ ፕሮጀክቱ ሰባት ሞጁሎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ሳምንት ሶፍትዌሩ እንዴት ይሰራል በሚል በእያንዳንዱ ሞጁል ላይ ለሰልጣኞቹ ማሳያና ገለፃ የተደረገ ሲሆን በሁለተኛው ሳምንት ደግሞ የማጠቃለያና የግምገማ ጊዜ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡ ፕሮጀክቱ ካለው ሰባት ሞጁሎች መካከል አምስቱ መጠናቀቃቸውንና ተግባራዊ ለማድግ መፈራረም የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የገለፁት አቶ አክሊሉ በስልጠናው ወቅት የተነሱ በሱፐርቫይዘሮች ሊመለሱ የማይችሉና ወደ ማኔጅመንት የሚሄዱ ጥያቄዎች መኖራቸውንም ጨምረው አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም የሰው ኃይል እጥረት በመኖሩና ሱፐርቫይዘሮቹ ለፕሮጀክቱ ሙሉ ትኩረት ሰጥተው መከታተል እንዳይችሉ ክፍተት እየፈጠረ መሆኑን ገልፀው ቅጥር እንዲፈፀምና የሰውሃል እንዲሟላ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ማቅረባቸውን አቶ አክሊሉ ገልፀዋል፡፡ የሶፍትዌር ኮንሰልታንት የሆኑት አቶ ሃፍቶም ገብረመስቀል በበኩላቸው የስልጠናው ወይም የፕሮጀክቱ ዓላማ ‹‹ዩኒት ፎር ቢዝነስ ወርልድ›› የሚባል ሶፍትዌር በመጠቀም የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ አሰራር ኮምፒውተራይዝድ በማድረግ ወደሲስተሙ ማስገባት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ፕሮጀክቱ አሁን ያለበት ደረጃ ሶፍትዌር ዲዛይን ላይ ነው ያሉት ኮንሰልታንቱ ዲዛይኑ እንዳለቀ ሶፍትዌሩ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን አሁን ስልጠናውን እየወሰዱ ያሉ ከየስራ ክፍሎቹ የተውጣጡት ሱፐርቫይዘሮች ለሶፍትዌሩ ተጠቃሚዎች ስልጠና ይሰጣሉ ብለዋል በተጨማሪም ሶፍትዌሩን ተግባራዊ ካደረግን በኋላ ኮንሰልታንቱ ለአጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡