የዜና መግለጫ

የአመራር ስልጠና ማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: የአመራር ስልጠና ማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ
የተጫነበት ቀን:  2/6/2018 3:40:43 PM
የዜናው አካል:  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬይሽን አካዳሚ አማካኝነት በ4 ዙር የሰጠው የከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራር የክህሎት ማበልፀጊያ ስልጠና የማጠቃለያ ውይይት ጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም በኢሌሌ ሆቴል ተካሄደ:: የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብርሀኑ በሻህ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ ማጠቃለያ መድረኩ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሮች በስልጠና ጊዜያቸው ባነሱት ጥያቄዎችና ሀሳቦች ላይ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስና የአየር መንገድን መልካም ተሞክሮ በየስራ ሂደቱ በመተግበር ውጤታማ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በመገምገም በተገኘው ተሞክሮ ወደፊት የተሻለ አሰራር በመተግበር ስኬታማ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በትጋት ይሰራል ያሉት ዶ/ር ብርሃኑ በስድስት ወራት ውሥጥ የአዲስ አበባ-ጅቡቲን የባቡር መስመር ርክክብ በመፈጸም ወደ አገልግሎት ማሥገባት መቻሉን እንደ ትልቅ ስኬት አንስተዋል፡፡ የ2010 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በኮርፖሬሽኑ ፕላኒንግ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሜላት ፀጋዬ የቀረበ ሲሆን የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ደረጃ፣የፋይናንስ አቋም ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ወደ አገልግሎት መግባት ፣ በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት አሰጣጥና የሊፍት ስራ መጀመር ፣የለውጥ ስራ ጥናት እስከ ቡድን ድረስ መሰራቱ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች፣በጥልቅ ተሀድሶ ወቅት የተነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት ጅምሮች መኖራቸው፣የባቡር አካዳሚ ግንባታን ለማስጀመር የተደረጉ ጥረቶች እንዳሉ፣ከአቻ ተቋማት ጋር ልምድ ልውውጥ መደረጉ ፣በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናት ድጋፍ ማድረግ መጀመሩ በጥንካሬ የሚገለፁ መሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን ያሉ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በተለይም የለውጥ መሳሪያ ስኮር ካርዶችን ወደ ግለሰብ በማውረድ በኩል እጥረት በመኖሩ በቀጣይ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ የአዋሽ-ወልዲያ /ሀራ ገበያ/ የባቡር ፕሮጀክት ፅ/ቤት ኃላፊ ኢንጅነር አብዱልከሪም መሐመድ በፕሮጀክት ፅ/ቤቱ ያለውን የተግባቦት/Communication/ ቁጥጥር፣የሪፖርት አቀራረብና ግምገማ ፣ የአቅም ግንባታ ሰራና የድረ-ገፅ የአሰራር ስርዓት በመልካም ተሞክሮነት አቅርበዋል፡፡ በአመራር ስልጠና ወቅት በፋይናንስና በጀት አመዳደብ፣በሰው ሀብትና የለውጥ ስራዎች፣በስልጣን ተዋረድ፣በኮርፖሬሽኑና በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አ.ማ ላይ መካከል ስላለው ልዩነትና አንድነት ጥቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው የነበረ ሲሆን በማጠቃለያው መድረክ በሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች መልስና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብርሀኑ በሻህ ሁሉም የኮርፓሬሽኑ አመራር ከልመና(ብድር) ተላቀን እንዴት ወደገንዘብ አመንጪነት ተቀይረን የባቡር ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም መስራት እናዳለብን ስትራቴጂያዊ አመለካከት ልንይዝ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ ከልማት ድርጅቶች ቀዳሚ መሆናችንን ተረድተን መልካም ተሞክሮ ከወሰድንበት አየር መንገድ ለመስተካከል ብቻ ሳይሆን ለመብለጥ ልንሰራ ይገባል በማለት እንደ አየር መንገድ ሰራተኞች በዩኒፎርማቸው እንዲኮሩ የሚያደርግ የብድን መንፈስ ለማምጣት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ሁሉም አመራር ሆነ ሰራተኛ መንገድ ላይ ከሚነዛ አሉባልታ እራሱን በመውጣት ለኮርፖሬሽኑ ብሎም ለአገር ምን አስተዋጽኦ ማድረግ እናዳለበት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬይሽን አካዳሚ የአመራር ክህሎት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቀመረዲን በድሩ በበኩላቸው የኢ.ም.ባ.ኮ አመራር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልምድ ለመካፈል ፈቃደኛ ሆነው ስልጠናውን መውሰዳቸው ምን ያህል ለመለወጥና የተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት መወሰናቸውን እንደሚያሳይ ጠቅስው ሁሉም ለራሱ ዋና የስራ አስፈጻሚ ሆኖ በባለቤትነት ስሜት የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የኮርፖሬሽን ልዕቀት ደረጃ ለመድረስ ኮርፖሬት ባህል እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ ቀመረዲን የኮርፖሬት ባህል እሴት ኮርፖሬት አመራር ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡