የዜና መግለጫ

ለኮርፖሬሽኑ መካከለኛ አመራሮች ስለጠና ተሰጠ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: ለኮርፖሬሽኑ መካከለኛ አመራሮች ስለጠና ተሰጠ
የተጫነበት ቀን:  11/28/2017 3:26:29 PM
የዜናው አካል:  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባቡር አካዳሚ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬሽን አካዳሚ ጋር በመሆን ለምድር ባቡር ኮርፖሬሽን 30 ለሚሆኑ መካከለኛ አመራሮች በ1ኛ ዙር በባቡር አካዳሚ የስልጠና አዳራሽ የአመራር ብቃት ስልጠና ሰጠ፡፡ የስልጠና ፕሮግራሙ ላይ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የባቡር አካዳሚ ተጠባባቂ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዓብይ ጌታቸው ኮርፖሬሽኑ አዲስ መዋቅር ተግባራዊ አድርጎ ወደስራ የገባ ሲሆን ይህን አዲስ መዋቅር ተግባራዊና ውጤታማ ለማድረግ የአመራር ክህሎትን ለማሳደግ፣ በጋራ ተባብሮ ለመስራትና አመራሩ ብቃቱን እንዲያጎለብት ለማድረግ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬሽን አካዳሚ ሲኒየር አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ማተቡ የኔሁን ይህ ስለጠና በመካከለኛ አመራር ላይ ያሉ ተሳታፊዎች የማኔጅመንትና የአመራር እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ብቃቶች እንዲኖራቸው እና ከዋናው አመራር የሚቀበሏቸውን መመሪያዎች ተግባራዊ የሚያደርጉበት ልምድና መናበብ እንዲኖር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም አቬሽን አካዳሚው በእነዚህ የስልጠና መስኮች ላይ ከሃምሳ ዓመት በላይ የካበተ የረዥም ጊዜ ልምድ ያለው በመሆኑና እየተጠቀመበት ያለውን አሰራር ለኮርፖሬሽኑ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የልምድ ልውውጥ መደረጉ የኮርፖሬሽኑን አሰራር ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚደርሰው አስገንዝበዋል፡፡ ስልጠናው ለተከታታይ አምስት ቀናት መሰረታዊ የማኔጅመንት ክህሎት እና በሌሎችም የአመራር ብቃቶች ላይ የሚካሄድ ሲሆን በመጨረረሻም በስልጠና የተገኘው ልምድ እንዴት ወደ ተግባበር እናውለው እና ምን ለውጥ ማምጣት እንችላለን የሚለው ቀጣይ ስራ መሆኑም በስልጠናው ላይ ተነስቷል፡፡ በተመሳሳይ ባለፉት ሳምንት ለኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬሽን አካዳሚ ስልጠና የተሰጠ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ በቀጣይም ሌሎች የኮርፖሬሽኑ መካከለኛ አመራሮች በ2ኛ ና 3ተኛ ዙር ስልጠና እንደሚሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡