የዜና መግለጫ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አሳንሰሮች በሂደት ሥራ ሊጅምሩ ነው


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አሳንሰሮች በሂደት ሥራ ሊጅምሩ ነው
የተጫነበት ቀን:  11/27/2017 10:11:46 AM
የዜናው አካል:  የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አሳንሰሮች በሂደት ወደ ሥራ እንደሚገቡ የተነገረ ሲሆን የልደታ ባቡር ጣቢያም በሚቀጥሉት 21 ቀናት ውስጥ ሥራ ሊጀምሩ እንደሚችሉ ተገለጿል፡፡ የአዲስ አበባቀላል ባቡር ትራንዚት ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ በአዲስ አበባ ሰታዲዮም የሚገኘውን የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ጣቢያ አሳነሰር ፍተሸና የሙከራ ሥራ በአካል በመገኘት የተከታተሉ ሲሆን አገልግሎቱም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ለህዝብ መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ከዝገጅት ክፍሉ ጋር በአደረጉት የስልክ ቆይታ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ጣቢያዎች ያሉ የአሳንሰር አገልግሎት ተገቢውን የደህንነት ፍተሻ እየተደረገላቸው እና መሥራታቸው እየተረጋገጠ በሂደት ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተናግረው በቀጣይም በእቅድ ተይዞ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚው በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ አሳንሱሮች በቅድሚያ ሥራ እንደሚጀምሩ አስታወቀው በእስጢፋኖስ፣በሜክሲኮ፣በለገሃር፣በመገናኛ፣በምኒሊክ አደባባይ ሚገኙ አሳንሰሮች በቀጣይ በሚደረግ የፍተሸ እና የሙከራ ማረጋገጫ ወደ ሥራ የሚገቡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የአሳንሰሮቹ አገልግሎት ለጊዜው ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት እንደሚሆን አቶ አወቀ አሰፋ የተናገሩ ሲሆን በሂደትም ሰው የሚበዛበት ቦታ እየታየ የአቅመ ደካሞችን እና የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችን እንቅስቃሴ በማይገድብ መልኩ የአገልግሎት ሰዓቱ እንደሚረዛም አመላክተዋል፡፡ የአሳንሰሮቹ አገልግሎት ያለምንም ችግር የባቡር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች እንዲገለገሉባቸው እና የደህንነትም ችግር እንዳይፈጠር የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በየባቡር ጣቢያው ባሉ አሳንሰሮች ድጋፍ የሚደርግ የሰው ኃይል ያዘጋጀ መሆኑን ኃላፊው ተናግረው በቀጣይም የሰው ኃይል ችግር እንዳይፈጠር ተቋሙ በዘርፉ የሰለጠነ ብቁ የሰው ኃይል እንደሚያሟላ አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም የልደታ ባቡር ጣቢያን ወደ ሥራ ለማስገባት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት በኩል ያለው ሂደት የተጀመረ መሆኑን ኃላፊው ተናገረው በአካባቢው ከሚገኘው የህንጻው ባለቤት ጋር በደህንነት ድንበር አወሳሰን፣የመብራት አጠቃቀም እና የህንጻውን በሮች በምን መልኩ እንደሚጋሩ እና በሌሎች ተዛማች ጉዳዮች ላይ ውል ለመፈራረም በሂደት ላይ መሆናቸውን አስታውቀው በቀጣይ ከሦስት እሰከ አራት ሳምንት ባለው ጊዜ ወደ ሥራ ሊገባ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ የባቡር ጣቢያው ቶሎ ወደ ሥራ ያለመግባት ምክኒያት ክህጻው ግንባታ ሂደት ጋር የተያያዘ በመሆኑና ግንባታው እሰከሚያልቅ መጠበቅ ስለአለበት መሆኑን ጠቅሰው ግንባታው ሙሉ ለሙሉ በመጠናቀቁ በፍጥነት የውሉ ሂደት አጠናቆ በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡