የዜና መግለጫ

የኮርፖሬሽን ሠራተኞች በዓመታዊ እቅድ እና የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ መከሩ


ዜናውን የዘገበው:
ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
የዜናው ምስል: የኮርፖሬሽን ሠራተኞች በዓመታዊ እቅድ እና የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ መከሩ
የተጫነበት ቀን:  11/16/2017 11:15:14 AM
የዜናው አካል:  የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እና የማኔጅመንት አባላት በኮርፖሬሽኑ 2010 ዓ.ም. እቅድ፣የመጀመሪያ እሩብ ዓመት አቅድ አፈፃጸም እና በመልካም አስተዳደር እቅድ ተወያይተው የፀረ ሙስና ስትራቴጂን አድምጠዋል፡፡ በሕዳር 02 ቀን 2010 ዓ.ም በጊዮዎን ሆቴል በተደረገው ስብሰባ የኮርፖሬሽኑ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ በሻህ ስለስብሰባው ዓላማ አስመልክተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ እንዳስታወቁት ስብሰባው ስለበጀት ዓመቱ እቅድ ሠራተኞች እና ኃላፊዎች ግንዛቤ የሚያገኙበት መሆኑን አመለክተው እቅዱ ለ25 መምሪዎች ተሸንሽኖ የተዘጋጀ እና ኃላፊነተቸውንም ጭምር ለየክፍሉ እና ለግለሰቦች የደለደለ በመሆኑ ከባለፈው ጊዜ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡ የዓመቱን እቅድ እና የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ያቀረቡት የእቅድ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሜላት ፀጋዬ በበኩላቸው የእቅድ ዝግጅቱ የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ፣የሁለተኛውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እና የሀገሪቱ ፖለሲዎችን መሰረት አድረጎ አንደተዘጋጀ ገልጸው አላማውም ጥራቱን የጠበቀ የባቡር መሰረተ ልማት ለመገንባት፣ ውጤታማ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመሰጠት፣የባቡር ዘረፍ አቅም ለመገንባት፣ጠንካራ የፋይናንስ አቅም ለመፍጠር እና የተቋሙን የአሠራር ስረአት ለማዘመን መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ወ/ሮ ሜላት ለመድረኩ ባቀረቡት እቅድ እንዳስታወቁት በበጀት ዓመቱ የአዋሽ-ወልዲያ ሃራ ገቢያ ፕሮጀክትን 84% እንዲሁም የወልዲያ-መቀሌን ፕሮጀክት 64% አፈጻጸም ለማድረስ እቅድ እንዳለ ገልጸው ውጤታማ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የባቡር ደህንነት የማረጋገጥ እና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ጥራት ለመጠበቅ እና የአዲስ አበባ-ጅቡቲን የባቡር አገለግሎት ወደሥራ የማስገባት ሥራ እንደሚሰ,ሠራ ተናግረዋል፡፡ በባቡር አካዳሚ ዘርፍ የሰው ኃይል አቅም በስልጠና ለማብቃት አንደታቀደ ገለጸው በምርምር እና ስርጸት ውጤቶችን ለመተግበር እንደሁም የባቡር አካዳሚ ለመገንባት በዚህ ዓመት እንደታቀደ ወ/ሮ ሜላት ተናግረዋል ገቢን ለማሳደግ የቀላል ባቡርን በሙሉ አቅሙ የመጠቀም፣ለዉጪ ተቋራጭ የሚወጣውን በሀገር ውስጥ የሰው ኃይል በመተካት ወጪን ቅነሳ እንዲሁም ሌሎች የገቢ ማሰባሰብያ ሥራ እንደታቀደ ተናግረው የኮርፕሬሽንኑን አሠራር ለማዘመን ISO፣ MIS እና IFRS በዚህ አመት ወደ ትግበራ እንድሚገቡ ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ እቅዱን ለመፈጸም የሚያስፈለገው ገቢ መጠን 64 ቢሊዮን ብር እንደሆነ አስታውቀው ከዚህ ውስጥ 44 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ 24 ቢሊዮን ከውጭ የብድር ተቋማት ለማግኘት የታቀደ ሲሆን የበጀቱ 46 በመቶ ለግንባታ፣ 23 በመቶ የብድር ክፍያ 13 በመቶ ለስራ ማስከያጃ እንደሚውል ወ/ሮ ሜላት አስረድተዋል፡፡ የሩብ አመቱን እቅድ አፈጻጸም በተመለከተ የዝግጅት ምእረፍ ላይ መሆናቸውን ኃላፊዋ አስረድተው የለውጥ ሰራዊት ግንባታ የሕዝብ ክንፍ እና የውጤት ተኮር አሠራር BSC ትግበራ ላይ ውስኑነት እንዳለ ተናግረው የመሥራያ ቤቱን አሠራር ለማዘመን የሚደረገው ጥረት በመልካም ጎኑ ተጠቅሷል በሩብ ዓመቱ ለዘጠኝ ሠራተኞች በቻይና ሀገር ሴሚናር እንዲካፈሉ እድል መመቻቸቱን እና ልምዳቸውን የሚጋሩበት መድረክ መዛገጀቱን፣ የ66 ተማሪዎች የማስተር ፕሮግራም ማጠናቀቃቸውን እና ቀሪ 24 ተማሪዎች በምረቃ ጹሁፍ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ወ/ሮ ሜላት ተናግረዋል፡፡ በእለቱ የጸረሙስና እስትራቴጂ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ጥናቱ የስጋት ቀጠናዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡