የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት በይፋ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የጀመረው መስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም ነው ሲሆን ይህም የቻይናው የባቡር ምህንድስና ኩባንያ የግንባታ ስራውን በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ውስጥ ካጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት:
• 34 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡
• ሁለት የጉዞ መስመሮች ያሉት ሲሆን አንደኛው የምዕራብ-ምስራቅ አቅጣጫን ተከትሎ ከአያት ወደ ጦር ኃይሎች አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የደቡብ-ሰሜን አቅጣጫ የጉዞ መስመር ደግሞ ከቃሊቲ እስከ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
• ሁለቱ መስመሮች 2.66 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የጋራ መስመር ሲኖራቸው ከስታዲዮም እስከ ቅድስት ልደታ ያሉትን ጣቢያዎች ያካትታል፡፡

• 41 ባቡሮች ያሉት ሲሆን ለተሳፋሪዎች አጠቃቀም ምቹ ለማድረግም በቀለማት እንዲለያዩ ተደርጓል፡፡ ሰማያዊ በነጭ ባቡሮች ከቃሊቲ እስከ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ ባለው መስመር እንዲሁም ከአያት እስከ ጦር ኃይሎች በተዘረጋው መስመር አረንጓዴ በነጭ ባቡሮች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
• ለመንገደኖች መሳፈሪያና መውረጃ አመቺ የሆኑ 39 ጣቢያዎች በመሬት ላይ፣ በዋሻ ውስጥ፣ በከፊል ዋሻ ውስጥና በድልድይ ላይ ይገኛሉ፡፡
• ደረጃዎች፣ አሳንሰሮችና ስካሌተሮች ለአካል ጉዳተኞችና ለአቅመ-ደካሞች አመቺ ናቸው፡፡
• ባቡሮቹ የጥገና አገልግሎት የሚያገኙባቸው ሁለት ዲፖቶች በቃሊቲና አያት ተገንብተዋል፡፡
• ቃሊቲ የሚገኘው ዲፖት ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመሆን ያገለግላል፡፡

ኦፕሬሽንና ጥገና

• ኦፕሬሽንና ጥገናው በሁለት የቻይና ኩባንያዎች ይተዳደራል፡፡ ሸንዘን ሜትሮ የአስተዳድር ስራውን በኃላፊነት ሲመራ የቻይናው ባቡር ምህንድስና ደግሞ የጥገና ስራውን ይመራል፡፡
• የደቡብ-ሰሜን አቅጣጫ ስራውን የጀመረው መስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም ሲሆን የምስራቅ-ምዕራብ መስመር ደግሞ ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም ነው፡፡

የወረቀት ትኬት

• በአሁኑ ወቅት በወረቀት ትኬት አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን ወደፊት የኤሌክትሮኒክስ ትኬት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

የጉዞ ዋጋ

• • 2 ብር እስከ 8 ጣቢያዎች
• • 4 ብር እስከ 16 ጣቢያዎች
• • 6 ብር እስከ 21 ጣቢያዎች

የትኬት መሸጫ ማዕከላት በመሳፈሪያ ጣቢያዎች በቅርብ ርቀት የተገነቡ ስለሆነ ትኬት ፍለጋ ረጅም ርቀት መጓዝ ሳያስፈልግ ገዝቶ መጠቀም ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ አቅጣጫዎች መጓዝ የሚፈልጉ ተገልጋዮች ከአንድ የትኬት መሸጫ ትኬቶችን ማግኘትይችላሉ፡፡
የአገልግሎት ጊዜያት
 በቀን ለ16 ሠዓታት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት

የሥራ ክፍሎች

1. ትራንስፖርት ዲፓርትመንት
የትራንስፖርት ዲፓርትመንት የባቡር ስምሪትን ከማስተባበር፣ መምራት፣ መከታተልና ወደ ተጠቃሚው ህብረተሰብ ባቡሮቹን ከማሰማራት ባሻገር የትኬት ሽያጭ አገልግሎት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
ስልክ፡- +251-114-708033

2. የባቡር ጥገና ማዕከል
ይህ ማዕከል የባቡር ጥገና የሚያከናውን ሲሆን ባቡሮቹና የግንባታ ተሸከርካሪዎች በአግባቡ እየሰሩ መሆናቸውን፣ የባቡር ትራፊክ ምልክቶችን፣ የግንኙነት መሳሪያዎችንና የኔትዎርክ ቁሳቁሶችን አጠቃላይ ትክክለኛ አሰራር ይከታተላል፡፡
ስልክ፡-251-114-708113

3. የባቡር ደህንነትና ፀጥታ ዲፓርትመንት
የቀላል ባቡርን ደህንነት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የጥገናና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ይሰራል፤ ማዕከላዊ በተማከለ ጥበቃ አመራር ስርዓትን ይፈጥራል፡፡
ስልክ፡- +251-114-708063

4. ኮሜርሻል ዲፓርትመንት
የመስሪያ ቤቱን ዓመታዊ፣ የመንፈቅ፣ የሩብ ዓመትና ወርሃዊ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡ የትኬት ቁጥጥር፣ የሃብት ልማት፣ የደንበኞች አገልግሎትና የኢንተርፕራይዝ ግብይት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
ስልክ፡-+251-114-70-80-67

5. የፋይናንስና አስተዳድር ዲፓርትመንት
የመስሪያ ቤቱን አጠቃላይ ስራዎች በጥራት ለማከናወን የፋይናንስ አቅርቦቶችን በወቅቱ ከማቅረብ ጎን ለጎን የአስተዳድራዊ ስራዎችን ያከናውናል፡፡
ስልክ ቁጥር፡-+251-114-70-80-87

6. የሰው ሃብት ልማት ዲፓርትመንት
ዲፓርትመንቱ ብቁ ባለሙያዎችን የመመልመልና የቅጥር ስራዎችን ከማከናወን ባሻገር የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ የሰራተኞችን ተከታታይ ውጤት ተኮር የስራ ምዘና ያከናውናል፡፡
ስልክ፡- +251-114-70-80-79

7. ሕዝብ ግንኙነት ዲፓርትመንት
ዲፓርትመንቱ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በውስጥና በውጭው ማህበረሰብ ዘንድ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ከመስራት ባሻገር በደንበኞቹ ዘንድ ተቀባይነትን ያተረፈ ታማኝ የትራንስፖርት አገልግሎትን ሰጪ ድርጅት ሆኖ እንዲገኝ ይሰራል፡፡ የዲፓርትመንቱ የመጨረሻ ግብ የመስሪያ ቤቱን መልካም ስም መገንባት ነው፡፡
ስልክ ፡-+251-114-708082

የተቋሙ ስልክ ቁጥሮች:
ጽ/ቤት = +251-114-708073
የሕዝብ ግንኙነት ዲፓርትመንት = +251-114-708082
የደንበኞች አገልግሎት፡- = +251-114-708090